በሦስተኛው የብሔራዊ ስታቲቲክስ ልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ ለፓርላማ አባላት ለውይይት ቀረበ

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባለፈው ሁለተኛው የአምስት ዓመት የብሔራዊ ስታቲቲክስ ልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ፣ በሶስተኛው አምስት ዓመት የብሄራዊ ስታቲስቲክስ ልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ እንዲሁም በአስር አመት ስታቲስቲክስ ልማት ሮድ ማፕ ላይ መስከረም 03/01/2014ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢሊሌ ሆቴል ከፓርላማ አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የፓርላማ አባል እና የበጀት፣ ፋይናንስና ገቢዎች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ  ክቡር አቶ ጩና ቡያ ተቋሙ የሚያወጣቸው መረጃዎች እንደ ሃገር ለሚዘጋጁ የአጭር፣ መካከለኛና ረጅም ጊዜ ዕቅዶችና ፖሊሲ ቀረጻ፣ ለጥናትና ምርምር፣ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ለንፅፅር ቁልፍ ግባአት በመሆናቸው ያላቸው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኤጀንሲው እንደ ሃገር የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ መሰረት አድርጎ ለቀጣይ አምስትና አስር አመታት የታቀዱ እቅዶች እንዲሁም የ2014ዓ.ም ዕቅድ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ከውይይቱ የሚገኙ አስተያየቶች ታክለውበት ወደ ቀጣይ ምዕራፍ እንዲገባ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ እንደሆነ በማስረዳት ውይይቱን አስጀምረዋል፡፡

በዕለቱ ባለፉት አምስት ዓመታት የብሔራዊ ስታቲቲክስ ልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ ሥር የተሰሩ ዋና ዋና ስራዎች እና ያጋጠሙ ችግሮች፣ የቀጣይ አምስት ዓመት የብሄራዊ ስታቲስቲክስ ልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የአስር አመት ስታቲስቲክስ ልማት ሮድ ማፕ እንዲሁም የ2014ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ቀርቦ በተሳታፊች ውይይትና አስተያየት ተሰትቶበታል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያም ተቋሙ የሀገሪቱን ስታቲስቲክስ መረጃ ፍላጎት ለማሟላት እስካሁን ያከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ቋሚ ኮሚቴው እውቅና ይሚሰጡት ተግባር እንደሆነ፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት ለመተግበር የተዘጋጀው የሦስተኛው አምስት አመት ስታቲስቲክስ ልማት ስትራቴጂ ስኬታማነትም ለተቋሙ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲሰጥ አዲስ ለሚተኳቸው የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ በቂ ማብራርያ እንደሚደረግላቸው የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ገልጸው ውይይቱ ተጠናቋል።

በውይት መድረኩ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ከፍተና አመራሮች እና 30 የፓርላማ አባላት ተሳትፈዋል፡፡