የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እና የ23ቱም ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊዎች ከሃምሌ01/2013ዓ.ም-መጋቢት30/2014ዓ.ም በዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ከሚያዝያ 05-07/2014ዓ.ም በአዳማ ድሬ ሆቴል ውይይት አካሄዱ፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ሲሆኑ ተቋሙ በ2014ዓ.ም በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ መሰረት ዘርፈ ብዙ ተግባሮችን ሲያከናውን መቆየቱንና የተዘጋጀውን ዕቅድ በክትትልና ድጋፍ ታግዞ በተያዘለት ጊዜ እና ጥራት መፈጸሙን በመገምገም የተሰሩ ጠንካራ ስራዎችን ለማስቀጠልና በበጀት አመቱ የታዩ ጉድለቶችን ለቀጣይ እንዳይደገሙ ለማሻሻል የተዘጋጀ የውይይት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በውይይት መድረኩ የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የሃብት ምዝገባ ገለጻ፣ የዳሬክቶሬቶች የስራ ሂደት ሪፖርት እና የዘጠኝ ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በተያዘው በጀት አመት የዳይሬክቶሬቶች የስራ አፈጻጸምና መረጃ ከማመንጨት አንጻር ተቋሙ ጥሩ አፈጻጸም ያስመዘገበ ሲሆን ከብሄራዊ ስታቲስቲክስ ፣ የተሽከርካሪ እጥረት፣ የኢንተርኔት ኮኔክሽን እጥረትና የውሎ አበል ማነስ እነደችግር ተነስተው በቀጣይ መፍትሄ እንደሚያገኙ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ምላሽ ተሰትቶበታል፡፡
ከሃምሌ 01/3013 እስከ መጋቢት30/2014/ዓ.ም በጀት አመት አጠቃላይ የተቋሙ አማከይ የዕቅድ አፈጻጸም 83% ሲሆን ከበጀት አንጻር 62% በበጀት አመቱ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡
በቀሩት ሦስት ወራት ወደኋላ የተቀረባቸው ዕቅድ ተግባራት ተለይተው ከፍተኛ ርብርበ በማድረግ ለማጠናቀቅ ጠንክሮ መሰራት እንደሚገባ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ በየደረጃው የሚገኘው አመራር የመረጃ ጥራትንና ወቅታዊነቱን ለማስጠበቅ አሁን ያለውና ጥሩ መነሳሳት አጠናክረው መቀጠል እንዳለበቸው የስራ አቅጣጫ በመስጠት የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡