የአገልጋይነት ቀን ተከበረ

ጷጉሜ1/2015ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አመራሮችና ሰራተኞች የአገልጋይነት ቀንን በፓናል ውይይት በተቋሙ የስብሰባ አዳራሽ አከበሩ።

የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ አግልጋይነት የሚጀምረው ከውስጥ ከተቋሙ የሚጀምርና ለውጪ ተገልጋዮች የሚደርስ ትህትና፣ ቅንነት፣ ታማኝነትን መላበስ የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን ገልፀው ተቋማችን አገልግሎት ሰጪ ከሚባሉ ተቋማት አንዱ በመሆኑ የሙያ ባህሪያችን አብዝቶ የሚጠይቀውን ትህትና በመላበስ ህዝባችንን ለማገልገል መዘጋጀት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዕለቱን በማስመልከት የተዘጋጀ ጽሁፍ ገለፃ ቀርቦ ፓናል ውይይት የተደረገበት ሲሆን በውይይቱም የተቋሙ አንጋፋ ባለሙያዎች ለወጣት ባለሙያዎች ከአገልጋይነት ልምዳቸው በማካፈል እንዲሁም ወጣቶች የሚረከቡትን ተቋም እንዴት ለማገልገል እየተዘጋጁ እንደሆነ አስተማሪ ሀሳቦች የተነሱበትና ግንዛቤ የተፈጠረበት ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም በተቋሙ የተለየ የአገልጋይነት ስብዕና አላቸው ተብለው የተለዩ ሁለት አንጋፋ ሰራተኞች ሽልማት በማበርከት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።