የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ

ጥር 27/2015ዓ.ም የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ የሆኑት ሶስት ተቋማት የተሳተፉበት የስድስት ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከረዩ ሪዞርት ተካሄደ።

አንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት በሚል እሳቤ የተዘጋጀው የአራቱ ተቋማት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የፕላን ሚኒስቴርና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ነመራ ገበየሁ በተገኙበት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

ባለፉት ስድስት ወራት በአራቱ ተቋማት የተሰሩ ስራዎች እንደየተቋማቱ የዕቅድ ስፋት የተለያዩ ቢሆኑም ጥሩ አፈፃፀም እንደነበራቸው በውይይቱ ላይ ተነስቷል።የውይይቱ ተሳታፊዎች በተፈጠረው መድረክ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው የጋራ መድረኩ መቀጠል እንዳለበት አስረድተዋል።

በመድረኩ የአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር ጠቃሚና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አራቱ ተቋማት በዛ ያሉ በጋራ መሰራት ያለባቸው ሀገራዊ ጉዳዮች እንዳሉ በመረዳት በቀጣይ ቅንጅታዊ አሰራሮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው የመካከለኛ ዘመን ስትራቴጂክ ዕቅድና የየተቋማችን ፖሊሲና ሰነድ ማዘጋጀት እንደሚገባ ዶ/ር ነመራ ገበየሁ ቀጣይ ስራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።