ስድተኛው ዙር የቤተሰብ ተኮር የኑሮ ሁኔታ ክትትል ስታቲስቲክስ ጥናት የመሰረክ ስራ ለማስጀመር ዝግጅቱ ተጠናቌል

ስድተኛው ር የቤተሰብ ተኮር የኑሮ ሁኔታ ክትትል ስታቲስቲክስ ጥናት የመሰረክ ስራ ለማስጀመር ዝግጅቱ ተጠናቌል

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ስድስተኛውን ዙር የቤተሰብ ተኮር የኑሮ ሁኔታ ክትትል ስታቲስቲክስ ጥናት ለማካሄድ የመስክ ስራ የማስጀመር ፕሮግራም ታህሳስ 24/2013ዓ.ም በአዳማ ደምበል ቪው ሆቴል አካሄደ።

በፕሮግራሙ ላይ የተለያዩ የኤጀንሲው ከፍተኛ ሀላፊዎች፣ተጋባዥ እንግዶችና ስልጠናውን የወሰዱ መረጃ ሰብሳቢዎች በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል።

በእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት በሚኒስቴር ማዕረግ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ሀላፊ ሚኒስተር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የተገኙ ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ከተቌቌመበት ጊዜ አንስቶ የሀገሪቷን መረጃ ፍላጎት ለማሟላት በርካታ ጥናቶች ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀው ከነዚህ ጥናቶች ውስጥ የቤተሰብ ተኮር የኑሮ ሁኔታ ክትትል ስታቲስቲክስ ጥናት አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

የቤተሰብ ተኮር የኑሮ ሁኔታ ክትትል ጥናት ሁለት ትልልቅ ጥናቶች የያዘ ሲሆን የቤተሰብ ፍጆታ ና ወጪ ጥናትና የኢኮኖሚና ማህበራዊ ደህንነት ክትትል ጥናት ሲሆኑ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣የማህበራዊና ልማት ዕቅዶችን ለመንደፍ አፈፃፀማቸውን ለመገምገም፣ለመከታተልና አስፈላጊ የፖሊስ እርምጃዎችን ለመውሰድ መሠረታዊ በመሆናቸው በየአምስት አመት የሚካሄድ ጥናት መሆኑን ኮሚሽነሯ ተናግረዋል።

ጥናቱ በከተማ፣በገጠርና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሀገሪቱን የድህነት ወለል ለማስላት ወሳኝ መረጃ የሚመነጭበት ጥናት ሲሆን ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ጥናቶች መረዳት እንደሚቻለው ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ የሀገሪቷ ህዝቦች በመቶኛ አሃዝ በ1987/88 ዓ.ም፣በ1991/92፣በ1996/97፣በ2002/03 ና 2007/08 ዓ.ም በተደረጉት ጥናቶች ከድህነት ወለል በታች የነበሩት የሀገሪቱ ህዝቦች በቅድመ ተከተል 45.5%፣44.2%፣38.7%፣29.6%ና 23.5% በመሆን በየአምስት አመቱ የድህነት ምጣኔው በተከታታይ ቅናሽ ማሳየቱን መረጃው ያረጋጋጠ ሲሆን፤ይህም የሚያሳየው በአገሪቱ ሲተገበሩ የነበሩ ግዙፍ የልማት ፕሮግራሞች በቤተሰቦች ህይወት ላይ ጉልህ ለውጥ ማሳየታቸውን ነው፤ነገር ግን አሁንም ከድህነት ወለል በታች ያለው ህዝባችን ቁጥር ብዙ ሲሆን ዘርፍ ብዙ የሆነውን ድህነት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ ትልቅ ስራ ከፊታችን ይጠብቀናል ሲሉ ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ በአፅኖት ተናግረዋል።

የተለያዩ የልማት እንቅስቃሲዎች በአገራችን ህዝቦች ላይ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣታቸውን ለመገምገም በ2013/14 ዓ.ም ለማካሄድ የታቀደው የቤተሰብ ተኮር የኑሮ ሁኔታ ክትትል ስታቲስቲክስ ጥናት ወሳኝ መረጃዎችን የሚያስገኝ በመሆኑ በስራው ላይ የሚሳተፉ ሁሉ ለስራው መሳካት ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ በመሆናቸው በትጋት በታታሪነት ሀገራዊ ዜግነታቸውን እንዲወጡ የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

እጅግ ጠቃሚ መረጃዎችን የሚያስገኘው ጥናቱ ለማሳካት የክልል፣የዞን፣የወረዳ፣የከተማ አስተዳድሮች ና የቀበሌ መስተዳድሮች፣የሀይማኖት መሪዎች፣የጎሳ መሪዎች፣የሀገር ሽማግሌዎችና በአጠቃላይ የህብረተሰቡ ትብብር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው ሁሉም የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽነሯ ተናግረዋል።

በፌደራልና በክልል የሚገኙ የሚድያ ተቌማት የጥናቱን ጠቃሚነት ለህብረተሰቡ ለማስገንዘብ ና ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ተደጋጋሚ ትምህርትና ቅስቀሳ እንዲደረግ ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ጥርያቸውን አቅርበዋል።

መረጃ ሰብሰቢዎች ስራቸውን ሲያከናኑ በገጠር ሆነ በከተማ በተመረጡ የናሙና ቦታዎች ሲንቀሳቀሱ የጤና ሚኒስቴር ለኮቪድ-19 ያወጣቸውን መከላከያ መመርያዎችን በትክክልና በለማቌረጥ እንዲተገበር ጥሪ ቀርቧል።

በመጨረሻም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ከሰልጣኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን መረጃ ሰብሳቢዎች በታማኝነት ና በቅንነት መረጃ እንዲሰበስቡ ጥርያቸውን አቅርበው፣እስካሁን መረጃ ሰብሳቢዎች ባለመሰልቸት ና በቁርጠኝነት ስልጠናውን በመውሰዳቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ጥናቱ ከጥር 1/2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2014 ዓ.ም አመቱን በሙሉ ይካሄዳል።