የተቋሙ የአንደኛው ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

የማዕከላዊ ስተሰቲስቲክስ ኤጀንሲ ከፍተኛ አመራሮችና የ25ቱም ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊዎች በአንደኛው ሩብ አመት ዕቅድ አጻጸም ላይ ከህደር 8-10ዓ.ም በአዳማ ደንበል ቪው ሆቴል ግምገማ አካሄዱ።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ተቋሙ በየዓመቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና የሥነ-ሕዝብ መረጃዎችን ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም በቆጠራና በናሙና ጥናቶች ከመስክና ከአስተዳደራዊ መዛግብት በመሰብሰብ፣ በማጠናቀርና በመተንተን ሪፖርቶችን እያዘጋጀ ለመረጃ ተጠቃሚዎች የሚያቀርብ መሆኑን ገልጸው በ2014 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት በዕቅድ በመያዝ ከሐምሌ 01 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሲያከናውን መቆየቱንና የሩብ አመት አፈጻጸሙን መገምገም የተሰሩ ጠንካራ ስራዎችን ለመቀጠል እና በሩብ አመቱ የታዩ ጉድለቶችን ለቀጣይ እንዳይደገሙ ለማሻሻል እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ የዋናው መ/ቤትና የቅ/ጽ/ቤቶች ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በተያዘው ሩብ አመት የስታቲስቲክስ የህግ ማዕቀፉን ከማዘመንየመረጃ ልማትን ማስፋፋትጥራት እና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ከማመንጨት፣የተጣጣመ ስታቲስቲካዊ መረጃ አገልግሎት ብሄራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓቱን በሚገባ ከማስተባበር አንጻር ከፍተኛ ስራዎች ተሰርተዋል በተጨማሪም ሶስት ጥናቶች የመስክ ስራቸው የተጠናቀቁ ሲሆን ዘጠኝ ጥናቶች አሁንም በመሰራት ላይ እንደሆኑ ከቀረበው ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በአፈጻጸሙ ያጋጠሙ ችግሮችም የተሸከሪካሪዎች ሰርቪስ ጉዳይ፣የመሰክ መገልገያ ዕቃዎች እርጅናና እጥረትና በቅ//ቤቶች ውስጥ ራውቴር ከመቃጠሉ ጋር ተያይዞ ኢንቴርኔት አለመሥራት እንደችግር ተነስተው በቀጣይ መፍትሄ እንደሚያገኙ በሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ምላሽ ተሰትቶበታል፡፡

የ2014 በጀት አንደኛ ሩብ ዓመት የተቋሙ የዕቅድ አፈጻጸም 83% እንዲሁም ከበጀት አንጻር (69%) በሩብ አመቱ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

በመጨረሻም በቀረበው አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጎ በተቋሙ ከፍተና አመራሮች ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡