የኤጄንሲው የስታቲስቲክስ መረጃ ተደራሽ ለማድረግ ከመገናኛ ብዙሀን ጋር መሰራ እንዳለበት ተገለፀ፡፡

ኤጀንሲው የስታቲስቲክስ መረጃ ለመገናኛ ብዙሀን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ሚድያዎች የስታቲስቲክስ መረጃ ዋቢ አድርገው ህብረተሰቡን ከማስተማር አንፃር ያለው ልምድ ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ከኢትዩጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ጋር በ13/09/2013 ዓ.ም ባደረጉት ቃለመጠይቅ ገለፁ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ በቃለመጠየቁ እንደገለፁት የኤጀንሲው ዋና ተልኮ የስታቲስቲክስ መረጃ ማቀረብ፣ በሌሎች አካላት የሚወጡ የስታቲስቲክስ መረጃዎች ጥራት መቆጣጠርና የመከታተል እንዲሁም ሌሎች መረጃ አመንጪ አካላት ተፈላጊ መረጃዎች እንዲያመነጩ የማስተባበርና የመመምራት ተልዕኮ ይዞ የሚሰራ ተቋም መሆኑን በንግግራቸው የገለፁ ሲሆን በስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የሚወጡ ጥናቶች ለህብረተሱ ተደራሽ ከመሆን አንፃር ከመረጃ አመጪው መረጃ የመስጠት ክፍተትና የመገኛ ብዙሀን የስታቲስቲክስ መረጃ ተጠቅሞ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረግ ክፍትት መኖርን ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩ ሲሆን ይህን ክፍተት ለመቅረፍ የስታቲስቲክስ መረጃ በሚመለከት ጠንከር ያለ ህግ ወቶ የስታቲስቲክስ መረጃዎች ተደራሽ እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው እስካሁን ተቋሙ ትኩረት ይሰጥ የነበረው ለፖሊሲና ለልማታዊ ዕቅዶች ለመከታተል የሚረዱ መረጃዎችን ማውጣትና የተቋሙ ድረገፅ ላይ ከመጫን ውጪ ከመረጃ አጠቃቀም ላይ ያለውን ክፍትት ክትትል አድረጎ እንደማይሰራ አስታውሰው ነገርግን ስታቲስቲክስ መረጃ አስፈላጊና ጠቀሜታ በሚመለከት የህብረተሰቡን ግንዛቤ ከማሳደግና የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች ከማስተዋወቅ አንፃር ያሉብን ክፍተቶች ለማወቅ የሚያስችል የደንበኞች እርካታ ጥናት (user satisfaction survey) በገለልተኛ አካል የተጠና ሲሆን ከጥናቱ መረዳት እንደተቻለው ያሉትን ትክክለኛ መረጃ ተጠቃሚው በትክክል እንደማያውቃቸው እንዲሁም ትክክለኛው መረጃ ጥቅም ላይ መዋል ላይ ክፍተት መኖሩን ጥናቱ ማመለከቱን ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው ገልፀዋል፡፡

በኤጀንሲው በኩል የስታቲስቲክስ መረጃ የማሰተዋወቅ ስራ ላይ ያሉብንን ክፍተቶች ለመመለስ የሚያስችል የቀጣይ የአምስት አመታት የስታቲስቲክስ ኮሚኒኬሽንና አድቮኬሲ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር ለመግባት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ዋና ዳሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

በዚህ ስትራቴጂ ውስጥ አንዱ ትኩረት ተቋማሙ ከሁሉም አይነት የመገናኛ ብዙሀን አማራጮች ጋር  ያለው ግንኙነት የበለጠ በማሻሻል የሚወጡ የስታቲስቲክስ መረጃዎች ለመገናኛ ብዙሀን ተደራሽ ማድረግ ብቻውን በቂ ስላልሆነ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች ስለስታቲስቲክስ መረጃ አዘጋገብ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ቀጣይና ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ሥራዎች ትኩረት ተሰጦ ለመስራት ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡ እንዲሁንም የስታቲስቲከስ ካላንደር ተዘጋጅቶ ጥናቶች መቼ እንዲሚወጡ የሚያሳይ ካላንደር የማዘጋጀት ስራ እየሰተሰራ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡

የመገናኛ ብዙሀን የስታቲስቲክስ መረጃን የመጠየቅ ልምድ ዝቅተኛ ሲሆን ለዚህ ደግሞ እንደ ክፍትት የሚገለፀው በኤጄንሲው የተዘጋጀ የስታቲስቲክስ ካላንደር ባለመኖሩ የመገናኛ ብዙሃን በትክክል መተው ስለተለያዩ ስታቲስካዊ መረጃዎች ጠይቀው ስለማይሰሩ የስታቲስቲክስ መረጃን የመገናኛ ብዙሀን በአግባቡ ተጠቅመው የመስራት ክፍትት መኖሩን ዋና ዳይሬክተሩ በንግግራቸው ገልፀዋል፡፡

በኮቪድ-19 ወረርሽን አማካኝነት በ2012 ዓ.ም ሊካሄዱ የነበሩ ጥናቶች ሳይካሄዱ በመቅረታቸውን በ2013 ዓ.ም ሁሉም ጥናቶች የጤና ሚንስቴር ባወጣው መመርያ መሰረት ጥንቃቄ በማደረግ ሁሉን ጥናቶች ከወረቀት ንኪኪ ነፃ በማደረግ በታብሌት መረጃዎች እንዲሰበሱ መደረጉን ገልፀው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአጠቃላይ በዜጎች ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ አመላካች መረጃዎች ለማግኘት በሁሉም ጥናቶች ላይ መጠይቆችን በማካተት መረጃዎች እየተሰበሰቡ እንደሚገኙ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቢራቱ ይገዙ ገልፀዋል፡፡