የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ሰነድ ላይ ስልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የሚተገበር የኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ለመግባት ከዋና መስርያ ቤትና ከቅ/ፅ/ቤት ለተውጣጡ 50 ለሚሆኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች በአዳማ ዶሻ ሆቴል ከመጋቢት 8-13/2014ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የህዝብ ግንኙነትና መረጃ ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሳፊ ገመዲ ሲሆኑ ተቋሙ ያለበትን የውስጥና የውጭ የኮሙዩኒኬሽን ክፍተት ለማሻሻል የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወነ ሲሆን ከነዚህ ተግባራት መካከል ለተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዎች ግንዛቤ በመፍጠር በትግበራው የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ ያለመ ስልጠና መስጠት ሲሆን በቀጣይ በእያንዳንዱ ተቋሙ በሚሰራቸው ጥናቶች ላይ የሚካተት ሰርቬ ኮሙኒኬሽን ማኑዋል በማዘጋጀት ለመረጃ ሰብሳቢዎች ግንዛቤ በመፍጠር ተቋሙን በማስተዋወቅ ስራ ላይ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችል የኮሙዩኒኬሽን መመሪያ መዘጋጀቱን ገልፀው በቀጣይ ግብዓት በመውሰድና መመሪያው ላይ በማካተት ወደ ትግባር እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ የተቋሙ ኮርና ደጋፊ የስራ ሂደቶች ላይ ያለው ውስጣዊ ተግባቦት ክፍተት በመኖሩ በቀጣይ የተሻለ የኮሙዩኒኬሽን ሂደት እንዲኖር በጋራ በመስራት እንደሚኖርበት ተገልጿል፡፡

በስልጠናው የኮሙዩኒኬሽን ፅንሰ ሀሳብ፣ የኮሙዩኒኬሽን ሰነድ፣ሰርቬ ኮሙዩኒኬሽን መመሪያ፣ በተቋሙ ሎጎና ብራንዲግ ትርጉምና ተግባራት፣ የሚድያ ላይ ቃለምልልስ ሲደረግ መደረግ የሚገባቸው ተግባራትና የተቋሙ የመረጃ ስርጭት ፍላት ፎርሞችና ላይ ገለፃ የተሰጠ ሲሆን በተለያዩ የመወያያ ርዕሶች ላይ በቡድን በመወያየት የስልጠናው ተሳታፊዎች ያላቸውን ሀሳብና አሰተያየት አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻ በስልጠናው ተሳታፊዎች በርካታ ገንቢ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በቀጣይ ተቋሙ ያለበትን ውስጣዊና ውጫዊ የኮሙዩኒኬሽን ከፍተት ለመሙላት ሁሉም ሰልጣኞች የኮሙዩኒኬሽን አንባሳደሮች በመሆን ተቋሙን ለማስተዋወቅ በሚሰሩ ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እንደሚያደረጉ በመግለፅ ስልጠናው ተጠናቋል፡፡