የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባዘጋጀው የሪፎርም መነሻ ሰነድ ላይ ሰራተኞች ተወያዩ

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ባዘጋጀው የሪፎርም መነሻ ሰነድ ላይ ከኤጀንሲው የዋናው መ/ቤት ሠራተኞች ጋር ታህሳስ 21-23 በተቋሙ የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄደዋል፡፡

 የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ውይይቱን በንግግር ሲከፍቱ እንደገለፁት ከመንግስት ና ከህዝቡ የሚነሱትን ጥያቄዎች በተገቢው መልኩ መመለስ የሚያስችል ተቋማዊ አደረጃጀት ላይ ሪፎርም መደረግ እንዳለበት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ተቋማችንም አሁን ከሀገራችን ዕድገት ጋር ተያይዞ እየጨመረ ያለውን የመረጃ ፍላጎት እንዲሁም ቀጣይ ረዘም ላሉ አመታት የሚኖረው ፍላጎት ማስተናገድ የሚያስችል ተቋማዊ ሪፎርም ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ዛሬ ለሠራተኞችን ውይይት የቀረበው የመነሻ ሰነድ በዚሁ ተግባር በተቋቋሙ የሪፎርም ኮሚቴ አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን ኮሚቴው ተቋሙ አሁን ያሉትን እጥረቶች/gaps/ እንዲሁም የመፍትሄ ሐሳብ /Recommdation/ በመለየት ለውይይት እንደቀርበ አስረድተዋል፡፡በቀጣይ ሪፎርሙ ተግባራዊ ሲደርግ ሠራተኛው በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ና የተግባሩ ባለቤት ስለሆኑ አሁን ጅምር ላይ የሚገኘው የተቋሙ ሪፎርም ሰነድ ላይ በጥልቀት በመወያየት ያልተካተቱ እጥረቶች እንዲሁም ፤የመፍትሄ ሀሳቦች በግልጽ በማንሳት የሪፎረም ሰነድ ሙሉ ና ረዘም ላሉት አመታት ተቋሙ ልሄድበት የሚያስችለውን አቅጣጫ የሚያመላክት የማድረግ ሀላፊነት ያለባችው መሆኑን አውቃችው በውይይቱ ላይ ሁሉም በመሳተፍ ለሰነዱ የሚያስፈልጉትን ግብዓት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል፡፡

የተዘጋጀውን የሪፎርም መነሻ ሰነድ ገለጻዎችን የኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተርና የሪፎርም ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ት አበራሽ ታሪኩ ና በሌሎችም የኮሚቴ አባላት የቀረቡ ሲሆን አሁን ተቋሙ ካለበት ደረጃ መነሳት እንደእጥረት/gaps/ የተለዩ አስር መሰረታዊ ጉዳዮች ተብለው የተለዮት የመረጃ አቅርቦት እጥረት/Data gap/፣የመረጃ ጥራትና ተደራሽነት፣የቴክኒክና ፋይናስ አቅም፣የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣መስተባበር፣ተቋማዊአደረጃጀት፣የስታቲስቲክስ ህግ እንዲሁም የኮሚኒኬሽን ና አድቮኬሲ ሲሆኑ በቀረቡት መነሻ ገለጻዎች ሰራተኞች ሰፊ ሙያዊ ውይይት በማድረግ ና ግብአቶች የሚሆኑ ሀሳቦች ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይም አሁን የተገኙትን ሀሳቦች በማካተት በመጨረሻው ሰነድ ላይ ውይይቶች ከሰራተኞች ና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚያደርጉ በውይይቱ መዝጊያ ላይ የተገኙት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር በመግለፅ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡