የተቀናጀ የመረጃ ተደራሽነት ስርዓት (IMIS) አጠቃቀም ይፋ ተደረገ

የተቀናጀ የመረጃ ተደራሽነት ስርዓት (IMIS) አጠቃቀም ይፋ ተደረገ

በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የተቀናጀ የመረጃ ተደራሽነት ስርዓት (Integrated management Information system (IMIS) በቢሾፍቱ ሊሳክ ሪዞርት ከታህሳስ 15-16/ 2013 ዓ.ም ስርዓቱን የማስተዋወቅና ይፋ የማድረግ ፕሮግራም ተካሄደ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኤጀንሲው የስነ-ሕዝብና ቫይታል ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አሳልፈው አበራ ይህ የተቀናጀ የመረጃ ተደራሽነት ስርዓት መረጃን አመቺ በሆነ መልኩ (user friendly በሆነ መንገድ ለተጠቃሚዎች ባሉበት ቦታ ሆነው መጠቀም የሚያስችል ስርዓት እንደሆነ ገልፀዋል። ይህ የመረጃ ማሰራጫ ስርዓት መረጃዎችን ከአንድ የመረጃ ቋት/data base/ ማሰራጨትና መጠቀም የሚያስችል ስርዓት ሲሆን የክልሎችና የሀገር አቀፍ መረጃዎችን ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ የተቀናጀ የመረጃ ተደራሽነት ስርዓት (Integrated management Information system (IMIS) በማስተዋወቅ መረጃ ተጠቃሚዎች ይህ ስርዓት መኖሩን ግንዛቤ አግኝተው እንዲጠቀሙበት ነው ተብሏል። ይህ ስርዓት በአሁኑ ጊዜ በአማራ፣ በትግራይ፣ በደቡብ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣በአፋር ክልል ሴክተር መ/ቤቶች እየተጠቀሙበት ሲሆን የመረጃ ስርጭት ስርዓቱ በሁሉም የፌዴራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች እንዲጠቀሙበት ለማድረግና ስርዓቱን ለማስተዋወቅ እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል። የተቀናጀ የመረጃ ተደራሽነት ስርዓቱ በብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት ውስጥ ያሉ ተቋማት መረጃዎችን በአንድ የመረጃ ቋት ለማግኘት እንደሚረዳ ተገልጿል።

የተቀናጀ የመረጃ ተደራሽነት ስርዓት (Integrated management Information system (IMIS)  የማስተዋወቅና የስልጠና ፕሮግራም ከብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት ተቋማትና ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ስልጠናው ተሰጥቷል። በስልጠናው መዝጊያ ላይ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢራቱ ይገዙ ይህ ስርዓት መረጃን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ በሁሉም የፌዴራል፣ የክልልና ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች የመረጃ ስርጭቱ ስርዓት አካል መሆን ብቻ ሳይሆን ወደ ተግባር በማስገባት ለልማት እቅድና ክትትል ማዋል እንዳለባቸው አሳውቀዋል። ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በዚህ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ድጋፍ በማድረግ ከሚገኘው ከUNFPA ጋር በመሆን በቀጣይ አስፈላጊው የስልጠናና የቴክኒክ እገዛ ማድረጉን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ ያለብንን የመረጃ ክፍተቶች ለመሙላት በጋራ መስራት አለብን በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።