የዓለም የሴቶች ቀንን የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ አከበረ

በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለ110ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ45ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የሴቶች ቀን ‹‹የሴቶችን መብት የሚያስከብር ማህበረሰብ እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማቱ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ እና የፓሊሲ ጥናት ኢኒስቲትዩት ሠራተኞች ጋር በጋራ በመሆን በፕላን እና ልማት ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ የካቲት 29/2013 ዓ.ም አክብሯል፡፡

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ገረመው ነጋሳ መድረኩን በንግግር  የከፈቱ ሲሆን በንግግራቸው የዘንድሮው የዓለም የሴቶች ቀን ‹‹የሴቶችን መብት የሚያስከብር ማህበረሰብ እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል የሚከበር መሆኑን ጠቅሰው በዓሉ የዓለም ሴቶች ለመብታቸው መከበር ያደረጉትን ትግል የሚዘክሩበት፣ በሴቶች በኩል የታዩ መሻሻሎች የሚንጸባረቁበትና ለሴቶች ብርታትና ቁርጠኝነት ዕውቅና የሚሰጠበት ዕለት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሴቶችን ብቁ ማድረግ ሀገርን ማሳደግ ነው ያሉት አቶ ገረመው ነጋሳ ይህን ለማድረግ የሴቶች ብቻ ሳይሆን የወንዶች ሀላፊነትም ከፍተኛ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

የዘንድሮ የዓለም የሴቶች ቀን የአንድ ቀን በዓል ሳይሆን የካቲትን ወር በሳምንት በመክፈል የመጀመሪያውን ሳምንት የአመራር፣ ቀጣዩን የትምህርት፣ ሶስተኛውን የኢኮኖሚና አራተኛውን የፀረ-ፆታ ጥቃት ሳምንት በማለት ወሩን ሙሉ እንደሚከበር በዕለቱ በገልጿል፡፡

በመጨረሻም የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማቱ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ እና የፓሊሲ ጥናት ኢኒስቲትዩት ሠራተኞች ጋር በሴቶች ጉዳይ  በቀጣይ መሰራት ስላለባቸው ስራዎች ውይት ተደርጎ ክብረ በዓሉ ተጠናቋል።