የፕላን ልማት ኮሚሽንና ተጠሪ መስሪያ ቤቶች የ2012 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ላይ ተሳተፉ

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ፣ የፕላንና ልማት ኮሚሽንና የፖሊሲ ጥናትና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮችና  ሐምሌ 29/2012 ዓ.ም የችግኝ መትከል መርሀ ግብር አካሄዱ፡፡ በመርሀ ግብሩ ላይ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነሯ ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ሀገራችን ኢኮኖሚ ባህሪ ከተፈጥሮ ጋር በጥብቅ የተያያዘ በመሆኑ ተፈጥሮው በሚገባ ካልተጠበቀ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ፣ የሀይል አቅርቦት ማሳደግ፣ ጤናማ የሆነ ከባቢ አየር መፍጠር አይቻልም። በመሆኑም መንግስታችን ይህንን በመረዳት ካላፈው ዓመት ጀምሮ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም መጀመሩን ያስታወሱት  ኮሚሽነሯ በዚህ ዓመትም 5 ቢሊየን ችግኝ በመላ ሀገራችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል። እኛም የዚህ ዘመቻ አካል ነን በማለት ፕሮግራሙን አስጀምረዋል። በዚህ ክረምት የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ፣ የፕላንና ልማት ኮሚሽንና የፖሊሲ ጥናትና ኢንስቲትዩት 120,000 ችግኝ ለመትከል ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት ይህን እቅድ ለማሳካት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

ያለንበት ጊዜ አለም አቀፍ  ወረርሽኝ የሆነው ኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ባለበት ጊዜ በመሆኑ ተከላውን ስናደርግ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ መሆን እንዳለበት በመግለፅ የችግኝ መርሀ ግብሩን አስጀምረዋል።