በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት “ኢትዮጵያ ታመስግን” መርሃግብር ተካሄደ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሞያዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) የተላለፈውን መልክት ተከትሎ “ኢትዮጵያ ታመስግን” መርሃግብር ሀምሌ 21/2014 ዓ.ም በተቋሙ የስብሰባ አዳራሽ አካሄዱ፡፡

መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አማረ ለገሰ ሀገራችን ባለፉት አመታት ቀላል የማይባሉ ፈተናዎች እንደገጠሟትና ፈተናዎቹ በፈጣሪ እርዳታ ስላለፉ ማመስገን እንደሚገባ ገልጸው ከፈተናዎች ባሻገር በአለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያ መልካም የሚባሉ ስራዎችን የሰራችበት አመት በመሆኑ ለአምላክ ምስጋና ማቅረብ ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ም/ዋ/ዳሩ አያይዘውም የኢትዮጵያን ክብር በዓለም ላይ ከፍ ላደረጉ አትሌቶች ምስጋናን አቅርበው ከአትሌቶቻችን አንድነት፣ ጽናትና ትዕግስትን በመማር ሁላችንም ለሀገራችን ድል የበኩላችንን እንወጣ ብለዋል፡፡

በዕለቱ የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ለአንድ ደቂቃ ለፈጣሪ ምስጋናን ያቀረቡ ሲሆን በየኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በጋራ ተዘምሮ መርሃግብሩ ተጠናቋል፡፡