የቆጠራ ካርታን ወቅታዊ ለማደረገግ እየተሰራ ነው

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የቆጠራ ካርታን ወቅታዊ ማድረግ የሚያስችል ስልጠና ለ58 መረጃ ሰብሳቢዎች፣ 8ተቆጣጣሪዎችና 2 ቴክኒካል አስተባባሪዎች ከየካቲት 06/22014ዓ.ም እስከ የካቲት 10/2014ዓ.ም በአዳማ ፓንአፍሪክ ሆቴል ስልጠና ሰጠ፡፡

የቆጠራ ካርታው ሲዘጋጅ በአንድ ቆጠራ ቦታ በገጠር ከ 100 እሰከ 150 ቤተሰቦችን የሚይዝ ሲሆን በከተማ ደግሞ ከ150 እስከ 200 ቤትሰቦችን ያካትታል፡፡ በተጨማሪም አንድ ቀበሌ ከአንድ በላይ የቆጠራ ቦታዎች ሊኖሩት እንደሚችል በስልጠናው ተገልጿል፡፡ የተዘጋጀው የቆጠራ ካርታ አምስት አመት ያለፈውና በነዚህ ጊዜያት በሃገሪቱ የተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ የአሰፋፈር፣ የግንባታና መሰል ለውጦች የተከሰቱ ሲሆን ተያይዞም በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች ደረጃም የመቀላቀል፣ የመከፋፈልና የሽግሽግ ሂደቶች አጋጥመዋል፡፡ ለዚህም ማሳያነት በ2010ዓ.ም በአዲስ አበባ 116 አካባቢ ወረዳዎች የነበሩ እንደሆነና በአሁኑ ወቅት ከ121 በላይ መሆናቸው ተነግሮ በሃገሪቱ ላይ በተደረጉት ዘርፈ ብዙ ለውጦች ምክንያት ቆጠራ ካርታን ወቅታዊ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ከተደረገው ስልጠና ለመረዳት ተችሏል፡