የታህሳስ ወር የእህል ዋጋ መጠነኛ ቅናሽ አሳይቷል

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት ሁኔታ መረጃ በታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ19.5 ከመቶ ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡ 

የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በማነፃፀር የሚገኘው ውጤት ወቅታዊ የዋጋ ግሽበት ሁኔታን የሚያሳይ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የምግብ ዋጋ ግሽበት የታህሳስ ወር 2ዐ12 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር በ22.7  በመቶ ጭማሪ አሳይቷ፡፡በያዝነውም ወር አብዛኛዎቹ የእህል ዓይነቶች (በተለይ ሩዝ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ገብስ እና ማሽላ) ዋጋ ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ ቅናሽ ታይቷል፡፡ የስጋ ዋጋ ጭማሪው ግን እንደ ቀጠለ ነው፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ የምግብ ዓይነቶች በተለይም ቲማቲም፣ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ጎመን፣ ካሮት፣ ቅቤ፣ የምግብ ዘይት እና ወተት አይብና ዕንቁላል ቅናሽ አሳይተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ያለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ዋጋ ከአሁኑ ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በንጽጽር ዝቅተኛ ስለነበር የዋጋ ግሽበቱ በያዝነው ወር ከፍ ብሏል፡፡  

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የታህሳስ ወር 2ዐ12 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀርም የ15.8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት በተከታታይ ጭማሪ እያሳየ ነው፡፡ ከምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይ ልብስና መጫሚያ፣ የቤት ኪራይ፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል)፣ የቤት ዕቃዎችና የቤት ማስጌጫዎች፣ የቤት መስሪያ እቃዎች፣ ህክምና እና ትራንስፖርት በተለይም የቤት መኪና ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው፡፡ በአጠቃላይ የታህሳስ ወር 2ዐ12 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር በ0.6 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ 

የዘንድሮው ከአምናው ተመሳሳይ ወራት የሸማቾች ዋጋ ኢንዴክስ ለውጥ ንጽጽር በአገር አቀፍ ደረጃ

  

ወርና በጀት ዓመት

የዋጋ ግሽበት ሁኔታ

Budget Year and months

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት

የምግብ ዋጋ ግሽበት

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት

General

Inflation

Food

Inflation

Non-Food

Inflation

ሐምሌ 2009-ሰኔ 2010

ዓመታዊ አማካይ

14.4

13.5

15.8

July 2017 – June 2018

(Annual Average)

ሐምሌ 2010-ሰኔ 2011

(ዓመታዊ አማካይ)

12.6

13.1

12.0

July 2018 – June 2019

(Annual Average)

መስከረም 2011

11.9

10.7

13.2

September 2018

ጥቅምት 2011

12.1

9.6

15.2

October 2018

ህዳር 2011

9.3

9.4

9.2

November 2018

ታህሳስ 2011

10.4

11.4

9.1

December 2018

ጥር 2011

10.9

11.5

10.2

January 2019

የካቲት 2011

10.9

10.7

11.2

February 2019

መጋቢት 2011

11.1

11.4

10.8

March 2019

ሚያዚያ 2011

12.9

14.5

11.0

April 2019

ግንቦት 2011

16.2

20.7

11.1

May  2019

ሰኔ 2011

15.4

19.8

10.2

June  2019

ሐምሌ 2011

15.5

20.0

10.3

July  2019

ነሐሴ 2011

17.9

23.0

12.0

August 2019

መስከረም 2012

18.6

23.3

13.1

September 2019

ጥቅምት 2012

18.6

23.2

13.4

October 2019

ህዳር 2012

20.8

24.5

16.4

November 2019

ታህሳስ 2012

19.5

22.7

15.8

December 2019