የጥቅምት ወር የአትክልቶች ዋጋ መጠነኛ ቅናሽ አሳየ

የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት ሁኔታ መረጃ በጥቅምት 2012 . የተመዘገበው አጠቃላይ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ጥቅምት 2011 . ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር 18.6 በመቶ ከፍ ብሏል። የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር በማነፃፀር የሚገኘው ውጤት ወቅታዊ ዋጋ ግሽበትን የሚያሳይ ሲሆን ከዚህም ውስጥ የምግብ ዋጋ ግሽበት የጥቅምት 2012 . ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር 23.2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ዋና ዋና የእህል አይነቶች ( በተለይ ጤፍ፣ ገብስ፣ ማሽላ፣ በቆሎና የስንዴ ዱቄት) እና የበሬ ስጋ የተጋነነ ባይሆንም በያዝነውም ወር የዋጋ ጭማሪው እንደቀጠለ ነው። ይሁን እንጂ አንዳንድ የምግብ ዓይነቶች በተለይም ቲማቲም፣ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ድንች፣ ጎመን፣ ካሮት፣ ምስር፣ ቅቤ፣ የምግብ ዘይት እና ወተት አይብና ዕንቁላል መጠነኛ ቅናሽ አሳይተዋል፡፡

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት የጥቅምት ወር 2012 . ካለፈው ዓመት ጥቅምት ወር 2011 . ጋር ሲነፃፀር 13.4 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች ዋጋ ግሽበት በተከታታይ ጭማሪ እያሳየ ነው። ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይ ልብስና መጫሚያ፣ የቤት ኪራይ፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጅ (ማገዶና ከሰል) የቤት ዕቃዎችና የቤት ማስጌጫዎች፣ የቤት መስሪያ እቃዎች፣ ህክምና እና ትራንስፖርት (በተለይ የቤት መኪና) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው፡፡

አጠቃላይ የጥቅምት ወር 212 . የዋጋ ግሽበት ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር 0.2 ከመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ 

 

የዘንድሮውና ከአምናው ተመሳሳይ ራት የሸማቾች ዋጋ ኢንዴክስ ለውጥ ንጽጽር በአገር አቀፍ ደረጃ

ወርና በጀት ዓመት

የዋጋ ግሽበት ሁኔታ

Budget Year and months

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት

የምግብ ዋጋ ግሽበት

ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት

General

Inflation

Food

Inflation

Non-Food

Inflation

ሐምሌ 2009-ሰኔ 2010

ዓመታዊ አማካይ

14.4

13.5

15.8

July 2017 – June 2018

(Annual Average)

ሐምሌ 2010-ሰኔ 2011

(ዓመታዊ አማካይ)

12.6

13.1

12.0

July 2018 – June 2019

(Annual Average)

ነሐሴ 2010

14.2

13.8

14.8

August 2018

መስከረም 2011

11.9

10.7

13.2

September 2018

ጥቅምት 2011

12.1

9.6

15.2

October 2018

ህዳር 2011

9.3

9.4

9.2

November 2018

ታህሳስ 2011

10.4

11.4

9.1

December 2018

ጥር 2011

10.9

11.5

10.2

January 2019

የካቲት 2011

10.9

10.7

11.2

February 2019

መጋቢት 2011

11.1

11.4

10.8

March 2019

ሚያዚያ 2011

12.9

14.5

11.0

April 2019

ግንቦት 2011

16.2

20.7

11.1

May  2019

ሰኔ 2011

15.4

19.8

10.2

June  2019

ሐምሌ 2011

15.5

20.0

10.3

July  2019

ነሐሴ 2011

17.9

23.0

12.0

August 2019

መስከረም 2012

18.6

23.3

13.1

September 2019

ጥቅምት 2012

18.6

23.2

13.4

October 2019