የተቋሙ የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ተገመገመ

ጥር 19/2015ዓ.ም የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስድስት ወራት አፈፃፀም ግምገማ በዋና መ/ቤት አደረገ።

የተቋሙ ዋና መ/ቤት ሁሉንም የስራ ክፍሎች ያሳተፈ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌበተገኙበት ቀርቦ ተገመገመ። የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ከነበረብን የበጀት እጥረት አንፃር የተሰሩ ስራዎች ጥሩ እንደነበሩ፣ በቀጣይ ቀሪ ጊዜያት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረን ያለንን በጀት ታሳቢ ያደረገ የዕቅድ ክለሳ እንዲደረግ፣ የታቀዱት የሪፎርምና መደበኛ ተግባራት በተሟላ መልኩ ለመፈፀም እንድንችል በየደረጃው ያለው አመራር የአመራርነት ሚናውን መወጣት እንዳለበት አቅጣጫ በማስቀመጥ ግምገማው ተጠናቋል።