የፕላንና ልማት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማት ሰራተኞችና አመራሮች ጋር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ተጠሪ ተቋማት ከሆኑት የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ እና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አመራሮች እና ሠራተኞች በጋራ በመሆን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 12/2013 ዓ.ም የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሄዱ፡፡

በደም ልገሳው ሥነ-ሥርዓት ላይ የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ፍፁም አሰፋን  ጨምሮ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የደም ልገሳ መርሀ ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

የደም ልገሳ መርሐ-ግብሩ “ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተደረገ ያለው ንቅናቄ አካል መሆኑን  የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር  ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ገፀዋል።

በደም ልገሳው ወቅት የተገኙት አመራሮች እና ሠራተኞች  ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ደም በመለገሳቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው የገለጹ ሲሆን፣ የህግ ማስከበር ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

በሀገራችን ሰላም ለማምጣት የትኛውንም ነገር የማድረግ ኃላፊነት አለብን ያሉት አመራር እና ሠራተኞቹ፣ ሀገር ስትደፈር መሥዕዋትነት ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውንም አክለው ገልጸዋል።